Amharic Movies

Search For Similar Forums  ·  Get A Message Forum  ·  Return to Website
Start a New Post      Board|Threaded
Author Comment
Post Master



Nov 1, 2006 - 8:07AM
Camparada

Romantic comedy by producer Letbeb Mekonin and Imagine Productions.
Birook Assefa



Dec 23, 2007 - 7:02AM
Re: Camparada

I want to know the producer of Camparada.
It is the best story.
Email  
addisqueen22



Jul 9, 2008 - 11:47AM
Re: Camparada

I don't think this movie would qualify as romantic comedy as the ending is very sad...I loved it...but I thought it was longer than it needed to be....it almost felt like it lacked focus as the story kept going in tangent with the supporting actors.... there were too many scenes that were added that were too long and didn't contribute to the story line (eg like the group of friends interacting...funny but unnecessary) ….all in all great movie
stif



Feb 18, 2009 - 12:05AM
Re: Camparada


ፊልም ካምፓረዳ
አቅረቢ መዓዛ ገሰሰው
ስክሪፕት ጽሀፊ እስክንድር ታደሰ
አከፋፋይ ናሆም ሬከርድስ
ደራሲና ዳይሬክተር ለጥበብ መኮንን
SHALOM VEDIO MEKELE
IMAGINE PRODUCTION


ገምጋሚ ፓስወርድ


ታሪክ፣

ካምፓራዳ ስለምንድን ነው?
ፊልምን አስመልክቶ እንዲህ አይነት ጥያቄ ሲነሳ መልሱ በጥቂት ዓረፍተ ነግሮች የታሪኩን ዋና መስመር (Story line) ቁጭ ሊያደርግ የሚችል መሆን አለበት። መልሱ የፊልሙን ታሪክ ዋና መስመር፣ ማለትም ፊልሙ ሊተርክልን የሚፈልገውን ዋናውን ቁም ነጌር የሚጠቁም ይሆናል። እና ካምፓራዳ ስለ ምንድን ነው ስንል ፊልሙን ያየ ሰው ሁሉ የሚሰጠው መልስ ከሞላ ጎደል አንድ አይነት መሆን አለበት።

ለምሳሌ ፣ ፌርስት ብለድ ጆን ጄ ራምቦ የሚባል ቬትናም ውስጥ ያገለገለ ወታደር ወደ ስቴትስ ከተመለሰ በሁዋላ እንድ ትንሽ ከትማ ውስጥ ገብቶ ከከተማይቱ ህግ አስከባሪዎች በተልይም ከሸሪፉ ጋር ባለምግባባቱ ምክንያት ግጭት ተፈጥሮ በሰውና በንብረት ላይ ስለሚያደርሰው ጥፋት ነው።

ሰማያዊ ፌረስ፣ አባይን እትንኖ ዝናብ በተፈለገው ቦታ እንዲጥል የሚቻልበትን ዘዴ ያጠና ምሁር ጥናቱን ተግባራዊ ለማድረግ ሲጥር፣ በእንጻሩ ለሆዳቸው ያደሩ ጥቂት ሰዎች ኣላማው እንዳይሳካ ስለሚያደርጉት ሸፍጥ ነው።

በዚህ መልክ የአንድን ፊልም ዋና የታሪክ መስመር መግለጽ ካልተቻለ፣ ታሪኩ ችግር እንዳለበት ነው የሚቆጠረው። የካምፓራዳን ዋና የታሪክ መስመር በዚህ መልክ ማስቀመጥ አስቸጋሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። አንዳንድ ተመልካቾች የዩንቨርስቲ ከምፓስ ህይወት እንዴት እንደሚመስል የሚያሳይ ፊልም ነው ሲሉት ሰምቻለሁ። ጸዲ እንኩዋን አልሰማች። ጸዲ ጸዳለ የምትባል ጉዋደኛዬ ነች። እስሱዋ ብትሰማ እኔን ከምፓስ ያደርገኝ ነበር የምትለው። የማይመስል ነገር ስትሰማ ሁሌ እንዲያ ነው የምትለው።

በነገራቸን ላይ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ አዲስ ስለሆንም ይሁን ወይም ግንባታው በሚገባ ስላልተጠናቀ የዩንርስቲ ከምፓስ ድባብ ገና የሰፈነበት አይመስልም። ሜዳ፣ ሳር፣ ቅጠል አላየሁበትም። ሰኮላር መሳይ ጺማም ሰው፣ ራሰ በራ ዲን ዝር አላሉበትም። ተማሪዮቹ ራሳቸው የሚሴሩት ሆነ የሚናገሩት የዛን አይነት ከፍተኛ የትምህርት ተቁዋም ተማሪዎች የሚያደርጉት አይመስልም።
ዩኒቭርስቲ ሲባል ለብዙዎች የቅድሞው የቀዳማዊ ሀይለ ሥላሴ ዩንቬርስቲ ነው ማነጻጸሪያቸው። ያ ተቅዋም በኢትዮጵያ ሶሾ ፖሊቲካዊ ሁነት ውስጥ በጎን ይሁን ክፉ ግን ከፍተኛ ሚና መጨወት የቻሉ ተማሪዎች ያፈራ ስለነበር ብአጠቃላይ ዩኒቬርስቲ ሲባል የሚታይው በክብር እይታ ነው። ከምምጅህራኑ ሆንከተማሪዎቹም የሚጠበቅ የእውቀት፣ የሀሳብ፣ የድርጊትና ንግግር ደረጃ አለ ብዬ አምናለሁ። በዚህ ፤እምነቴ እያለሁ ዶርሚታሪ ውስጥ እንደ ህጻን ቴዲ ቤር የሚያቅፉ ሴቶች ልጆች ሳይ በስልጣኔና በብስለት መሃል ያለው ልዩነት ተምታቶብኝ ነበር። ይህን ሰለ ፊልም ስቴጅ ዴኮና ስለሙድ ስዳስስ አንድ ቀን እመለስበታለሁ። አሁን ወደ ተንሳሁበት ወደ ታሪክ መስመር።

የታሪክ መስመር ማውጣጣት እንዳቃተኝ ተረድታ ነው መሰል ዋናዋ ገጸ ባህሪ ገሊላ ራስዋ ሹክ ያለችን ነገር አለ። ፊልሙ መጨረሻ ላይ፣ ዳኒ በመኪና አደጋ ከተለያት በሁዋላ፣ ሰዎችን እንደገና ማመን፣ ማፍቀር ቻልኩ የምተለው ነገር። ከዚህ በመነሳት ነው አንድ የታሪኩ መስመር ሊሆን ይችላል የሚባል ነገር በስንት መከራ ያውጣጣሁት።

ይኸው፣
ካምፓራዳ፣ አንዲት ለአቅም ሄዋን ያላደረሰች ልጅ በእንጀራ አባትዋ በመደፈርዋ ምክንያት በሰዎች ላይ እምነት አጥ
Email  
stif



Feb 18, 2009 - 12:09AM
Re: Camparada

ይኸው፣
ካምፓራዳ፣ አንዲት ለአቅም ሄዋን ያላደረሰች ልጅ በእንጀራ አባትዋ በመደፈርዋ ምክንያት በሰዎች ላይ እምነት አጥታ ስትኖር ከቆየች በሁዋላ፣ አንድ በእውነት የሚወዳት ልጅ በማግኘትዋ ሰዎችን እንደገና ማመንና ማፈቅር መቻልዋን የሚተርክ ፊልም ነው። ይሄ ነው የተሪኩ ወነ መስመር። የአንድ ፊልም የታሪክ መስመር ከተቀየስ በሁዋላ ዝርዝር ትረካው፣ ቃለ ባህሪያቱና ትልሙ በዚያ ዙሪያ ማጠንጠን አለበት።

ካምፓራዳ ውስጥ የታዩት ዋና ዋና ትይንቶች በዋናው የታሪክ መስመር ዙሪያ ያጠነጠኑ ናቸውን? በርድ ምን ትየለሽ? ለመሆኑ ፊልሙን አይተሽዋል?

ይቀጥላል።

መልካም ገና

በነገራቸን ላይ ፊልምና መጽሀፍ ቆንጆ የገና ስጦታ ናቸው ይባላል፣ ምን ያህል እውነት ነው? አንዳዶቻችን ስጦታን የምንለካው በገንዝብ ነው፣ ውድ እቃ ካልሆነ ደስ አይለንም። ፍቅራችንን በሚገባ የገለጽን አይመስለንም። ይሄ ተዲያ ትክክል ነው ትያለሽ፣ በርድ?

ባለፈው አመት ለጉዋድኛዬ የስጠሁትን ልንገርሽ። ባለ ፈር የበርዶ ኮፍያ ነበር። ዋጋው ወደ 50 ዶላር ነው። እሱ ያመጣልኝ ግን የ10 ዶላር መጽሀፍ ነበር። የጤናማ ምግቦች አስራር የሚያስረዳና የሚያሳይ መጽሀፍ። ከመቶ በላይ የሚሆኑ ሪሳፕ ይዞአል። ቤት ውስጥ እስከሁን እንጠቀምበታለን። ቦርጭ ጀምሮኝ ነበር፣ የቆመው ከዚያ በሁዋላ ነው። እኔ የሰጠሁት የበረዶ ኮፍያ ግን ከሰቀለበት ቁምሳጥን ወጥቶ አያውቅም። ከመጽሀፍ የሚበልጥ ስጦታ ታውቂ እንደሆን፣ በርድ ንገሪኝ።




ካምፓራዳ ውስጥ የታዩት ዋና ዋና ትይንቶች በዋናው የታሪክ መስመር ዙሪያ ያጠነጠኑ ናቸውን? የሚል ጥያቄ አንስቼ ነበር። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ዋና ዋና ትይንቶች ከሚባሉት ውስጥ አንድ ሁለቱን አንስቼ ማገላበጥ ይኖርብኛል።
መጀምሪያ ላይ የሶሻል ሳይንስ መምህሩ ለተማሪዎቹ ሰጥቶአቸው የነበረ የቡድን ሥራ በደንብ እንዳልተሰራና በሌላ ርእስ እንደገና እንዲጽፉ ሲያዘቸው የነበርውን የክፍል ውስጥ ትይንት እወስዳልሁ። ይህ ትይንት ዋናዎቹን ገ/ባህሪያትና መቸቱን ከሞላ ጎደል ያስተዋውቆአል። የዳኒና የገሊላ የሚገናኙት እዚህ ትይንት ውስጥ ነው። የትይንቱን ሰፊ ጊዜ የያዘው የመምህሩ ንግግር ነው። በዚህ ንግግሩ ውስጥ ከታሪኩ ዋና መስመር፣ ማለትም በሚያምኑትና በሚወዱት ሰው ስለ መደፈር ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የነካካው ነገር እንዳለ እስኪ እንመልከት።
Email  
stif



Feb 18, 2009 - 12:12AM
Re: Camparada

ካምፓራዳ ውስጥ የታዩት ዋና ዋና ትይንቶች በዋናው የታሪክ መስመር ዙሪያ ያጠነጠኑ ናቸውን? የሚል ጥያቄ አንስቼ ነበር። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ዋና ዋና ትይንቶች ከሚባሉት ውስጥ አንዱን፣ ማለትም የትምህርት ክፍል ውስጥ ትይንትን ከዚህ በፊት በተቀመጠው ጽሁፍ ውስጥ አስነብቤአለሁ። ቀጥሉ የሬስቶራንቱ ትይንት በአጭሩ እዳስስና ከዋናው የታሪክ መስመር ዙሪያ መጠንጠኑን እንመረምራለን።

የሬስቶራንቱ ትይንት በሁለቱ ማለትም በዳንኤልና በገሊላ መሀል የስሜት መለዋወጥና መገናኘት የታየበት፣ ዳኒኤል ውስጡን ገልጦ ለገሊላ ያሳየበት ነው። ስለ ጉዋደኛው ስለሜሮን አንስቶ፣ በመሀላቸው መግባባት እንደሌለ ሁሉ ይገልጽላታል።
"የኔና የሜሮን ቴስት በጣም የተለያይ ነው።" የሚለው እዚህ ትይንት ውስጥ ነው።

ከዚህ በሁዋላ ራት ቀርቦ እየበሉ ስለምግብ አሰራርና ጣእም እያውሩ የዳንኤል እናት ስልክ ይደውሉና ያቁርጣቸዋል። እዚህ ላይ ይመስለኛል ገሊላ ራስዋ ስለቤተስቦችዋ የምታስበው። በዚህ ሀሳብ ውስጥ አስቃቂው ትዝታዋ ይመትጣል። ያ የምትወደውና የምታምነው አባትዋ፣( እንጀራ አባትዋ፣) አስገድዶ ሲደፍራት ይታያታል። ይህ በልጅነት ጊዜ ያሳለፍችው የስቃይ ህይወት ካደግችም በሁዋላ አለመሻሩንና አዲስ ህይወት፣ አዲስ ግንኙንት በሞከርች ቁጥር ከትዝታዋ መህደር እያፈተለከ ስላምና ጤና እንደሚነሳት እናውቃለን። ግን ይህን የምናውቀው በጣም ዘግይቶ ነው። ፊልሙ ተገባድዶ 60ኛ ደቂቀ ውስጥ ከገባን በሁዋላ። በመሰረቱ የዋናው ገጸባህሪ ዋና ችግር የፊልሙ መግቢያ ክፍል ውስጥ መቅረብ ነበረበት። ይህ ማለት ካምፓራዳ 110 ደቂቃዎች የሚወስድ ፊልም እንድመሆኑ መጠን በመጀመሪያው 30 ደቂቆች ውስጥ ማሳየት የነበረበት ትይንት መሃል ላይ አድርጎታል። ከዚህ በሁዋላ የሚቀረው የ 50 ደቂቃ ጊዜ ታሪኩን በተገቢው መንገድ ለመጨረስ ስለማይበቃ ደራሲው ገጽባህሪየትን ባልተጠብቀ ድንገተኘ አደጋ ማጥፋትና ታሪኩን ማቆም ይጋደዳል። ዳኒኤል የድንገተኛ መኪና አደጋ ሰልባ የሆነው በዚህ ምክንያት ማለት ይቻላል።

የፊልምና የልቦለድ ደራሲያን ታሪካቸውን በመግቢያ፣ ማበልጸጊያና መደምደሚያ ከፋፍለው የሚያቀርቡ ከሆነ፣ መግቢያና መደምደሚያው እኩል ገጻት ሲይዙ ማበልጸጊያው ማለትም መሀሉ የሁለቱን ድምር ገጻት ሊይዝ እንደሚገባ የሙያው ምሁራን ያሰተምራሉ። በዚህ መሰርት የካምፓራዳን ታሪክ ብንከፋፍለው ዳንኤልና ገሊላ ፍቅር ሲጀመሩ እንዲሁም ገሊላ በህጻንነትዋ የደረስባት የስነ ልቦና ምት በማህበረዊና በፍቅር ህይወትዋ ላይ ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ በመግቢያው ውስጥ ማሳየት መቻል ይገባዋል። ያን አድርጎ ቢሆን ኖሮ ፊልሙ መበልጸጊያ ክፍል ውስጥ ገሊላ ከችግሩዋ ለመውጣት፣ ከውስጥ ህመምዋ ለመዳን የተለያይ ህክምናና ርዳታ ስትሞክር የማሳያ ጊዜ ባገኘ ነበር።
Email  
stif



Feb 18, 2009 - 12:15AM
Re: Camparada

የታሪኩ ጭብጥ ትምህርተዊና ወቅተዊነትም ያለው የህብረተሰብ ችግር ነው። ሴቶች ልጆች በሚያምኑት ሰው፣( አባት፣ ወንድም፣ መምህር ወዘተ) ተገድደው የመደፈራችውን ያህል በማያውቁትና በማይወዱት ሰው ክብረ አንስታይነታቸውና ስብእናቸው እስኪፈርስ ይደፈራሉ። የካምፓራደ ደራሲው፣ ከዚህ በስብእና ላይ የሚደረግ አስቀቂ ወረራ በሁዋላ ሴቶች ልጆች የሚደርሰባቸውን የስነ ልቦና መታወክና የአእምሮ ቀውስ በሚገባ አጥንቶ በትረካው ውስጥ ቢያካትት ኖሮ ፊልሙ እጅግ ትምህርተዊና በኢትዮጵያ ፊልምና ልቦለዶች ያልተዳስስ አዲስ አድማስ ባሳየን ነበር። የፊልሙ ታሪክ አላማ ችግሩንና መፍትሄውን ማሳየት ለህብረተሰቡ ማሳየት እስከሆን ድረስ፣ በተመሰሳይ ችግር የሚሰቃዩ ሴቶች መፍትሄ መኖሩን እንዲያውቁ እስከሆነ ድረስ ደባብሶ ማለፉ ትርጉም የለውም።

ገሊላ የደረስባት በደል በአብዛናው ህይወትዋ ላይ ችግር ሲያስከትል እይታይም። በትምህርት ጎበዝ ነች። አንጋገርዋ በሳል ነው። ራስዋን ትጠብቃለች። የደረሰበት ግፍ ሊያስከትል የሚችለውን የስነ አእምሮ ችግር እንዴት እንደተጋፈጠችው ግልጽ ባይሆንም የተረዳችው በመንፈሰዊ ሀይል እምነት ይመስላል። ቤተክርስቲያ ተሰላሚነትዋን አሳይቶናል። አልያ ግን ተመሳሳይ በደል የሚደርስባቸው ሴቶች አስቸኩዋይ ርዳታ ከላገኙ ህይወታቸው ለመበላሸት ያለው እድል ስፊ መሆኑን ነው የማውቀው። ከተስፋ መቁረጥና ራስን አሳንሶ ከማይት የሚመነጭ የእጫሽነት፣ የጠጭነትና የአምንዝራነት አባዜ ይጠናወትዋል እንጂ እንድ ገሊላ አይነት ባህሪ ሊወጣቸው የለው እድል ኢምንት ነው።

የፊልሙ ሁለተኛው ክፍል፣ ማለትም ማበልጸጊያው ከላይ የጠቀስኩትን ችግር የሚዳስስ ቢሆንና ዳንኤል ከዚህ ችግር የምትወጣበትን ሳይንሰዊ ብልሀት ቢያመላክታት ወይም የስነልቦና ሳይንስ ምሁር ዘንድ ቢወስዳትና በመጨረሻ የሱ ፍቅር በታከልበት ሁኔታ ስትፈወስ የምናይበት ቢሆን የታሪኩ ዋና መስመር ሀዲዱን ሳይለቅ ከፍጻሜው ደረስ እል ነበር። ገሊላ ላይ የደረሰው በደል ዳንኤልን ለማፍቀር እምብዛም ኣላስቸገራትም። ካላስቸገራት ደግሞ ደራሲው በገሊላ ላይ የደርስባትን በድል አቃሎታል ማለት ነው። ይህ መስረታዊ ስህተት ነው። የታሪኩን ዋና መንስኤ ማቃለል የታሪኩን ከብደት ይዞት የሚወርድ አጉል ስህተት ነው። ገሊላ የደረስባት በደል በዳንኤልና በእስዋ መሀል ላለው ፍቅር እንቅፋትነቱ ጎልቶ መታየት ነበረበት ነው የምለው።
ይህን የምለው ፊልም ሰሪው ያቀደው ትክክል አይደለም፣ የኔን ቢስራ ይሻለዋል ለማለት እይደልም። እህስ? ፊልሙ ገሊላ ላይ የደረሰውን በደል ካሳየን ዘንዳ በደሉ የሚያስከትለውንም ችግር ማሳየት የግድ ስለሆነ ነው። የፊልሙ ታሪክ ደግሞ ገጸባህሪዋ ከዚያ ችግር የምትወጣበትን መንገድ ማሳየት ይሆናል። ጋቢቶ።
Email